ጉርዳ ከተመሰረተ ካንድ ዓመት በላይ ሆነው። በኢትዮጵያም ውስጥ ዕውቅና አግኝቶ ለመሥራት የሚያስፈልጉትን ነገሮች በማስፈፀም ላይ ይገኛል። ይህን መልዕክት ስጽፍላችሁም ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የሚመጣውን የድጋፍ ደብዳቤና መረጃ እየተጠባበቅን ሳለ ነው። ያንን ተቀብለን ወደ ኢትዮጵያ ኤምባሲ እንወስድና ኤምባሲው በሚሰጠው መምሪያ መሠረት ወዳገር ቤት ተልኮ ውሳኔውን በአንክሮ እንጠባበቃለን። የመንግሥት ዕውቅና ለሁለት ነገር ይጠቅመናል። ፩)ጉርዳ በኢትዮጵያ እንዲሰራ ዕውቅና ያገኛል። ፪) በዚህም ምክንያት የጉርዳ ተቀዳሚ ፕሮጄክት አንድ ሥራ ላይ ይውላል። የጉርዳ ፍላጎት በፍጥነት ፈቃድ አግኝቶ ሥራ መጀመር ቢሆንም የተዘጋጀውን መመሪያ አለመረዳታችንና የቦርድ አባላት ፊርማ ስብሰባ ትንኝ ጊዜ በልቶብናል። አሁን ግን መሥመር እንደያዘና ቶሎ ፍፃሜ ሊያገኝ እንደሚችል ርግጠኞች ነን። ወንድሞችና አህቶች፦ የጉርዳ አመራር ወደ ፊት የሚያዘልቀውን እንጂ ወደ ኋላ የሚጎትተውን ከቶ አያስበውም። ቀን ከሌሊት የምንደክመውም የጉራጌ ህዝብ በራሱ ጥረት ራስ አገዝ የሆኑ ክንዋኔዎችን እንዲፈፅም ነው። ከዛም በላይ ራዕያችን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ጠንካራ ድርጅትን ለማቆም ነው። ይህ ራዕይም ብ ቸኛውና ዋነኛው የጉርዳ ጅማሬና ፍፃሜ የሆነ የማዕዘን ራስና መሠረት እንደሆነ የማያውቅ አባል እንደሌለ ተስፋ እናደርጋለን። በተለያዩ የመገናኛ መድረኮቻችንና በአባላት ስብሰባዎች ላይ ደጋግመንም እንደገለጽነው ፕሮጀክት አንድ የመጀመሪያ ወይም የመግብያ ፕሮጀት እንጂ የመደምደሚያ አይደለም። ገና ብዙ ፕሮጀክቶች ይጠብቁናል። ፕሮጀት አንድ መጀመሩና ፍጻሜ መድረሱ የማይቀር ነው። በሚያረካና ጠቃሚ ሊሆን በሚችል መልኩ መደረግ ያለበትን ሁሉ ከማድረግ ችላ አላልንም። ዘላቂነት ያለው አገልግሎት ሊሰጥ እንዲችልም ኃላፊነት የሚሰማውና ዓቅም ያለው በጉርዳ ዓላማ የሚያምንና በጋራ ስምምነት የሚሰራ ድርጅትም እያነጋገርን እንደሆነ አባላት እንድታውቁልን አንወዳለን። ፕሮጀክት አንድ ስኬታማ ከሆነና ተረካቢ ካገኘ የበለጠ ለመሥራትና የበለጠ ታማኒነትን ለጉርዳ እንደሚያመጣና ትልቅ በር ከፋች ሊሆን እንደሚችል አንጠራጠርም። ይህንኑ ለማየት አየደከምን ስለሆነ ከኛ ሆናችሁ የት ናችሁ? ምን ደረሳችሁ? በምን አንርዳችሁ? ይህን አንዲህ ብታደርጉት? አከሌን ብታናግሩት? አያላችሁ አበረታቱን። ከሁሉም በላይ ተመዝግባችሁ የወር መዋጮ የማትከፍሉ መክፈል ጀምሩ፥ መመዝገብ ያልቻላችሁም ደውሉልን አንረዳችኋለን። ያለነዳጅ መኪና አንደማይሽከረከር ጉርዳም ያለናንተ መዋጮ የትም አይደርስም። በተጨማሪም እንድትገነዘቡልን የምንሻው ሁለተኛ ሦስተኛና ሌሎች ፕሮጀክቶችን ለመሥራት ካሁኑ ገንዘብ መሰብሰብ ይኖርብናል። የጉርዳ የቦርድ አባላት የናንተን ስልክ ለማስተናገድ እየጠበቋችሁ ነው። ልንሰራ አንጂ ልንታይ ቦርዱን አልተቀላቀልንም። ከራሳችንም አልፈን ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን እናስመዝግብ። የአመቱን ሁለተኛ ግማሽ ጀምረናል። ክፊታችንም ብዙ ዝግጅቶች ይጠብቁናል። እንድትሳተፉና ሥራ እንድታግዙ እንጋብዛችኋለን። ወንድሞቼና እህቶቼ፥ የተሰራውን ከመቁጠር ብዙ ያለተሰራውን ማየት ይሻላል ያሉት አዝማች ይርጋ ገብሬ ድረታ ናቸው። አዝማች የጉራጌ ራሰ አገዝ ልማት ድርጅትን ለረጅም ዘመን የመሩና ዛሬም ሳይታክቱ ጉርዳን በኢትዮጵያ ለማጠናከር ታጥቀው የተነሱ አባታችን ናቸው። በአገራችን ብዙ ያልተነኩ ነገሮች እንዳሉ ማየት ለሚችል ሁሉ ግልፅ ይመስለኛል። ብዙ ነገሮች አልተሰሩም። ይህን ያሉኝ የጉርዳ ቦርድ የኢትዮጵያ ተወካይ እንዲሆኑ ስለወሰነ ፈቃደኝነትዎን እየጠየቅሁ ነው በምልበት ጊዜ እሳቸውም ባጭሩ ይህ አስፈላጊ ሥራ ስለሆነ እኔም እሳተፍበታለሁ ብለው መለሱልኝ። ይህ ሥራ፥ ይህ የጉርዳ ሥራ ÷ቃል የገባንበት ሥራ ÷በጣም አስፈላጊ ሥራ ነው። ግን ማን ይስራው? Gurda:a promise worth keeping. Berhanu Zergaw Gurda President
0 Comments
Leave a Reply. |
Archives
January 2020
Categories |