logo

ይህ የጉርዳ የመጀመሪያው ፕሮጄክት፣ በቀድሞ አመራር ቦርድ በዕምድብር ከተማ የተጀመረና፣ የመጀመሪያው ምዕራፍ የመማሪያ ክፍሎች አንድ ብሎክ ህንፃ ተጠናቆ ፣ የሁለተኛውን ምዕራፍና የልዩ ድጋፍ ትምህርት አስጣጡን በቀጣይነት እንዲመራ ለተመረጠው የካቶሊክ ሚሺን ተራድኦ ድርጅት በተራዘመ ድርድርና ስምምነት አስረክበናል።

የቀድሞ የዕምድብር ትምህርት ቤት ተማሪዎችና ደጋፊዎች የትምህርት ቤቱን 50ኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ በአሰባሰቡት ድጋፍ ከጉርዳ ጋር በመተባበር የ ICT ማዕከል ለማቋቋም ዕቅድ ተጥሎ አፈፃፀሙ ያዘገመ ቢሆንም በቅርቡ የህንፃው ግንባታ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ተጀምሮ በመጠናቀቂያ ሥራ ላይ ይገኛል።

በዞን አስተዳደሩ በቀረበ ጥያቄ መሰረት ለ16 በዞኑ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የንፁህ የቧንቧ ውሀ አቅርቦት ለማስፈፀም፣ የስትራቴጂክ ዕቅዳችን ላይ ማስተካከያ በማድረግና በጀት በማደላደል የዕቅዱን ወጭ ለመሸፈን ተችሏል። በመሆኑም በሁሉም ትምህርት ቤቶች ንፁህ የቧንቧ ውሀ በማቅረብ በዕቅዱ መሰረት ተከናውኖ ትምህርት ቤቶቹን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

ጉርዳ ለወረርሺኙ ምላሽ ለመስጠት በውጭ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆን በማነሳሳት በተገኘ የገገዘብ ድጋፍ ከዞኑ የጤና መምሪያ ጋር በመነጋገር በሁሉም የዞኑ ቀበሌዎች ለሚገኙ የቀበሌ ጤና ኤክስቴንሺን ባለሙያዎች በወረሺኙ መከላከል የአቅም ግንባታ ስልጠና አግኝተው ወደ የቤት ለቤት የመከላከል ተግባር እንዲሰማሩ ተደርጓል። ቶቶት የተባለ የወጣቶች ማህበር በዞኑ ለሚደረግ ህዝባዊ ቅስቀሳ በቀረበው ዕቅድ መሰረት የማስፈፀሚያ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል። በተጨማሪም ለህክምናና የማግለያ ቦታዎች 200 ፍራሾችና እንሶላዎች ከአምራቾቹ በጨረታ ተገዝተው ለዞኑ አስተዳደር ተለግሷል። ከላይ የተጠቀሱት ተግባራት ከፍላጎቶቹና በውጭ ካለው የተወላጆች አቅም ጋር ሲመዘን እጅግ አነስተኛ አፈፃፀም እንደሆን ማብራሪያ የሚፈልግ አይሆንም። ምንም እንኳን የኮቪድ ወረርሺኝ፣ የሀገራችን ያልተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታ፣ የታቀዱ የልማት ተግባራትን ለማስፈፀም የሚያስፈልግ መዋለነዋይ ማሰባሰብ ላይ የነበረው ተፅዕኖ ከባድና ያልተቋረጠ ቢሆን የአመራር ብርሃን በአዳዲስ አቅም በመገንባት አዳዲስ ለልማት የሚውል ሀብት ለማሰባሰብ የተለያዩ ስልቶችን በመንደፍ መንቀሳቀስ ግዜ የማይስጠው ተግባር መሆን ይገባዋል።

በዞኑ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እንደያግዝ ታሳቢ ተደርጎ፣ ትምህርትን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በሚደረገው ጥረት በአረቅጥ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 50 የጠረጴዛ (desk top) ኮንፒዩተሮች ፣ በተጨማሪም የድሮዊንግ ቁሳቁሶች (drawing materials) ተገዝተው አስረክበናል። የእይሲቲ ማዕከሉም በሚገባ ተደራጅቶና ተመርቆ አገልግሎት ላይ ውሏል።

Our Maps

© 2024 Copyrights gurdainc. All Rights Reserved||Developed By Hex Labs